የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የትምህርት አጀማመርን አስመልክቶ መመሪያ ሰጥቷል።
በዚህም፦
1. የክረምት ሥራዎች እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2013 ድረስ እንዲጠናቀቁ፤
2. መምህራን ከጳጉሜ 1/2013 ጀምሮ ተገኝተው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቻቸውን እንዲያከናውኑ፤
3. አዲስና ነባር ያቋረጡ የተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 3 -7 /2014 ዓ.ም ድረስ እንዲከናወንና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ተፈጥረው ምዝገባው በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ፤
4. መስከረም 10/2014 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራ እንዲጀመር አሳስቧል።