የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ከ87 በመቶ በላይ ማለፋቸው ተገለፀ
በተያዘው አመት በአጠቃላይ 72 ሺ 544 ተማሪዎች የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ሲሆን 63 ሺ 812 ተማሪዎች ፈተናውን እንዳለፉ ተገልፆል፡፡
የፈተናው ማለፊያ 37 ነጥብ ሲሆን በዚህም ከ87.9 በመቶ የሚሆኑ ተፈታኞች ማለፋቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫለ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡