የትምህርት ሚኒስቴር በይፋዊ የማህበራዊ ገፁ ላይ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ፈተና ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይፋ ማድረጉን አስነብቧል።
የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ፈተናው ጥቅምት ወር ላይ እንዲሰጥ የተወሰነበትን ምክንያት እንደሚከተለው ዘርዝረዋል ፦
- በክረምት ወቅት ፈተና መስጠት አስቸጋሪ በመሆኑ
- ከፍተኛ የተፈታኝ ቁጥር በመኖሩ (ከ620,000 በላይ)
- ከተፈታኞች ብዛት አንጻር በቂ #የህትመት ጊዜ በማስፈለጉ
- በክረምት ወቅት ፈተና መስጠቱ ከስረጭት አንጻር ከ2,200 በላይ ወደ ሚሆኑ የፈተና ጣቢያዎች ፈተና ለማጓጓዝ እና ለማድረስ አመቺ ባለመሆኑ
- የትግራይ ተማሪዎች ጉዳይ፣
- የዩኒቨርሲቲ የቅበላ ጊዜ፣
- ክልሎች ፈተናውን ለመስጠት ያላቸው ዝግጁነት፣
- በመስከረም ወር ተደራራቢ በዓላት መኖራቸው
- የፌዴራልና የክልል የመንግስታት የምስረታ ወቅት በመሆኑ ፈተናው ጥቅምት አጋማሽ እንዲሰጥ ተወስኗል ብለዋል።
የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመቅረቱ በ2013 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ620 ሺ በላይ ተማሪዎች (99%) መመዝገባቸው ተገልጿል።
ይህም በ2012 ዓ/ም ለ አገር አቀፍ ፈተና ከተመዘገቡ 350 ሺህ ተማሪዎች በእጥፍ ያህል ብልጫ እንዳለው ነው የተነገረው።
መረጃው ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከNEAEA የተሰባሰበ ነው።