ለሁሉም የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመደቡ አዲስ ተማሪዎች በተለያዩ ምክንያቶች ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች በመመሪያው መሠረት የማስተካከያ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ለሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ቅሬታ ካቀረቡት ተማሪዎች መካከል የጾታ መቀያየር እና የትምህርት መስክ (Stream) መቀያየር ጥያቄ ያቀረቡ ተማሪዎች በተመደቡበት ተቋም እንዲፈታ እንዲደረግ የተወሰነ ስለሆነ የተማሪዎቹ ጥያቄ በተቋማቱ እንዲፈታ እናሳስባለን።