የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በቅርቡ ተግባራዊ የሚኾን አዲስ የሥርዓተ ትምህርት ይፋ አድርጓል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በቅርቡ ተግባራዊ የሚኾን አዲስ የሥርዓተ ትምህርት ይፋ አድርጓል፡፡
አዲሱን የሥርዓተ ትምህርት ይፋ ያደረጉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) ናቸው፡፡
በዚህም፦
- አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት በትምህርት ቤቶች አደረጃጀት ይለያል፦
° ከ1እስከ 6ኛ ያሉትን አንደኛ ደረጃ
° ከ7 እስከ 8 ያሉትን መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ፣
° ከ9 እስከ 12ኛ ያሉትን ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ በሚል ተደራጅቶ ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን አብራርተዋል፡፡
- የመምህራን ስልጠና ሥርዓትን በተመለከተ ከምልመላ ጀምሮ የስልጠና አይነት እና ጊዜ እንዲሻሻል ተደርጓል ብለዋል።
- ሥርዓተ ትምህርቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት እንዲኖረው የትምህርት ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ መደረጉን ጠቁመዋል።
- ሁለተኛ ደረጃ ላይ የትምህርት አሰጣጥ የቀለም ትምህርት እና የሙያ ትምህርት ተብሎ በሁለት መንገድ ሊሰጥ ታስቧል፥ ትግበራውም በቀጣይ ዓመት ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በተመረጡ ትምህርት ቤቶች፣ ከ7ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉ ኹሉም ትምህርት ቤቶች ተግባዊ ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ ነው ብለዋል።
- የማስተማሪያ ቋንቋን በተመለከተ በአማርኛ፣ በአዊኛ፣ በኽምጣና እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚኾን እና ሥርዓተ ትምህርቱም በዚሁ እንደሚዘጋጅ ገልጸዋል።
- የአርጎበኛ ቋንቋን ለማካተት የማጥናት ሥራ እየተሰራ እንደሆነ አንስተዋል።
- የግእዝ ቋንቋን በሥርዓተ ትምህርቱ ለማካተት ዝግጅት እየተደረገ እንደኾነም ጠቁመዋል።
(አሚኮ)