የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅያ (12ኛ ክፍል) ብሄራዊ ፈተና መደበኛና የማታ ተማሪዎች የሚመዘገቡት በ2012 ዓ.ም በመማር ላይ ባሉበት ትምህርት ቤት ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅያ (12ኛ ክፍል) ብሄራዊ ፈተና የግል አመልካቾች እና በርቀት ትምህርት የሚከታተሉ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በሚኖሩበት አካባቢ በሚገኘው የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሲሆን፤ በአዲስ አበባ የሚገኙት ግን በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ባሉባቸው የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ወይም ጽ/ቤቱ በሚያዘጋጀው የምዝገባ ጣቢያ
⚠️ማሳሰቢያ❗️
✅ምዝገባው የሚካሄደው በኦንላይ (Online) ሲሆን መደበኛና የማታ ተፈታኝ ተማሪዎች የሚመዘገቡት በ2012 ዓ.ም በመማር ላይ ባሉበት ትምህርት ቤት ይሆናል፡፡
✅ በተጨማሪም የኤጀንሲውን ዌብሳይት www.neaea.gov.et ወይም የኤጀንሲው ማህበራዊ ገጽ National Educational Assessment And Examinations Agency Government Organization ይጎብኙ፡፡
©ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ