የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት የተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ።
መውጫ ፈተና በሁሉም መደበኛና መደበኛ ባልሆኑ መርሀግብሮች የሚመረቁ ተማሪዎችን እንደሚመለከትና ፈተናውን በኦንላይን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ገልጸዋል።
የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከመደበኛ ተማሪዎች ባሻገር የማታና የርቀት ተመራቂ ተማሪዎችን እንደሚመለከት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ለመንግስትና ለግል ዩኒቨርስቲዎች የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ሲከፍቱ እንዳሉት መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚማሩ የቀን ፣የማታና የርቀት መርሀ ግብር ተመራቂዎች ይሰጣል።
ከዚህ ዓመት ጀምሮ በመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲዎች ተግባራዊ የሚደረገውን የመውጫ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት መታቀዱንም ዶክተር ሳሙኤል ጠቁመዋል።
በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የመሠረተ ልማት አቅሞቻቸውን ከወዲሁ በማረጋገጥ ለፈተናው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር ) በዚሁ ጊዜ ሲናገሩ የመውጫ ፈተና የትምህርት ጥራትን ከማስጠበቅ ባሻገር የተማሪዎችንና የተቋማቱን ብቃት ለማሳደግ እንደሚያስችል ጠቁመዋል።
በምክክር መድረኩ ሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተገኝተዋል።
በምክክር መድረኩም በመውጫ ፈተና ዙሪያ እየተደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት ፣ የመሠረተ ልማትና የ2015 ምሩቃን መረጃዎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።