የትምህርት ቤት የመመዝገቢያ ዋጋ ከወርሀዊ ክፍያ ከ25 በመቶ በላይ እንዳይበልጥ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱን የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን አስታውቋል።
የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ትምህርት ቤቶችን ለምዝገባ ከወርሀዊ ክፍያቸው በላይ እንዳያስከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር ነው።
ትምህርት ቤቶች ለምዝገባ ብቻ ከክፍያቸው በላይ እያስከፈሉ በማስቸገራቸው ምክንያት አሰራሩን መፈተሽ እንዳስፈለገ የጠቆሙት ዋና ስራ አስኪያጇ አዲሱ አሰራር ግን ለዚህ መፍትሄ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
እንደ ወይዘሮ ሸዊት ገለፃ፤ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሬን በሚመለከት ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በሚደረግ ስምምነት መሠረት እንደሚሆን ገልፀዋል። #ኢፕድ
#edu_news