ተማሪዎቹ እስከ ረቡዕ ሐምሌ ዐ7/2013 ዓ.ም ድረስ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንዲያደርጉ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል።
500 ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ሁለት ካምፓሶች
(በቱሉ አውሊያ 250 እና በመካነ ሰላም 250) መደልደላቸውን የተቋሙ የሬጅስትራር አስተባባሪ መንበረ ግርማ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።
በመሆኑም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ ቱሉ አውሊያ ካምፓስ እና የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በመካነ ሰላም ካምፓስ ሪፖርት ያድርጉ ብለዋል።
ዳግም ምደባ የተደረገላቸው አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦
• ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ
• 3×4 ፎቶግራፍ (8)
• ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ጨርቅ
• የስፖርት ትጥቅ
• የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ
ከተጠቀሰው ቀን ውጭ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ እንደማያስተናግድ የገለፀው ዩኒቨርስቲው፤ በዋናው ግቢ የተመደቡ ተማሪዎች አካባቢው ቀዝቃዛ ስለሆነ ወፍራም ልብስ እንዲይዙ መክሯል።