በጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ከ17 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን 186 የፈተና ጣቢያዎችና 523 ፈታኞች መዘጋጀታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሴ ጋጄት ተናግረዋል፡፡
ፈተናው በሚሰጥበት ቀንም ሆነ የፈተናው የጥያቄ ወረቀት የማጓጓዝ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲሆን በየዘርፉ የሚገኙ የፀጥታ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
መረጃው የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ነው።
Via Tikvah