የ2013 ትምህርት ዘመን የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከዛሬ ሚያዝያ 22/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይፋ ሆኗል።
በመሆኑም ተማሪዎች ከታች በተገለጸዉ የበየነ መረብ ጠቋሚ በመግባት የተመደቡበትን ተቋም ማወቅ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ዩኒቨርሲቲዎች
እስከ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን፡፡
• ዉጤት ለማየት መግቢያ ዌብሳይት፡-
http://result.neaea.gov.et/Home/Placement
• ቅሬታ ለማቅረብ መግቢያ ዌብሳይት (በአካል መምጣት አያስፈልግም)፡- http://moshe.gov.et/ ወይም https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7
አዲስ የዩኒቨርሲቲ ገቢ ተማሪዎች ወደ ተመደባችሁበት ዩኒቨርስቲ ስትሄዱ ወደ አዲስ የህይወትና ትምህርት ምዕራፍ ከመሻገር፤ ዕውቀትና ክህሎትን ከማካበት ባሻገር ህብረብሔራዊነትን፤ መቻቻልን፤ ወንድማማችነትን የምትኖሩበት፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ ባሕሎችን የምታዩበት፤ ለራሳችሁ እድል ከሰጣችሁ የተለያዩ ቋንቋዎችን የምትማሩበት እንዲሁም እጅግ የሰፋ
አመለካከትን ይዛችሁ የምትወጡበትና በጠቅላላ ወደ ትንሿ ኢትዮጵያ የምትቀላቀሉበት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ!
የፍሬሽማን ኮርሶችን ስትወስዱ ትኩረት በማድረግ በጥሩ ዉጤት እንድታጠናቅቁና ከሁለት ሴሚስተር ትምህርት በኋላ በበቂ መረጃና በዋናነት በመምህራኖቻችሁ ምክር ላይ የተመሰረተ የትምህርት ፕሮግራም እንደየአቅማችሁና ፍላጎታችሁ መርጣችሁ በመማር ብቁና በቂ ባለሙያ ሆናችሁ ለመመረቅ እንድትበቁ እንመኛለን።
ጠንካራ ስራ ለውጤት መሰረት ነው።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር