የካውንስሉን መመስረት ያበሰሩት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ
የሀገራችን ህዝብ ላለፉት 3 አስርት አመታት የትምህርት ጥራት ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቢቆይም ጥያቄው ሳይመለስ መቆየቱን ጠቅሰዉ አሁን ይህን የህዝብ ጥያቄ በአግባቡ መመለስ ግድ ያለበት ጊዜ ደርሰናል ብለዋል፡፡
ካውንስሉ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስርዓተ-ትምህርት ቀረጻና ማሻሻያዎች ላይ በመሳተፍ ብሎም ጥናትና ምርምር በማድረግ የማሻሻያ ሀሳብ በማቅረብ እንዲሁም የተቋማትን ደረጃ እስከማውጣት የሚደርስ ስራ የሚሰራ ይሆናል ሲሉ አባራርተዋል፡ካውንስሉ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ እንደሚሰራም ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ አረጋግጠዋል፡፡
በጉባኤው ምስረታ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስትር ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም በበኩላቸው ትምህርት የሰብዓዊ ልማት ማዕከል መሆኑን ገልጸው የዚህ ካውንስል መመስረት ህዝባችን ለሚፈልገው ሀገራዊ ልማት ፋይዳው እጅግ የጎላ ነው ብለዋል፡፡
ክብርት ፕሮፌሰር ቀጥለውም ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ማቅረብ ሀገርን ለመቀየር ካለው አስተዋጽኦ አንጻር ሲታይ ካውንስሉ ቀደም ብሎ መቋቋም ነበረበት እንደ ሙያ ማህበራትም ይሁን እንደዜጋ በዚህ መልኩ ተባብረንና ተቀራርበን ከሰራን ሀገራችን የምታልመውን ልማትና ስኬት ማረጋገጥ እንችላለን ሲሉ መክረዋል፡፡
የካውንስሉ አባላት የሆኑ የተለያዩ የሙያ ማህበራት ፕሬዚዳንቶች የካውንስሉ መመስረት ለትምህርት ጥራት መምጣት ካለው ፋይዳ አንጻር ጥሩ ጅምር እንደሆነ ገልጸው በሙሉ አቅም ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
Via S.H.E