ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦላይን ለመፈተን የሚያስችለውን አስፈልጊ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ለባለሙያዎች ስልጠናዎችን መስጠት የተጀመረ ሲሆን በትምህርት ቤቶችም ፈተናውን ለመስጠት የሚያስችል በቂ የመብራትና የኔትዎርክ አቅርቦት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በኦላይን የሚሠጠው ፈተና ኩረጃን ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ከመሆኑም ባሻገር ለወረቀትና ፈተናውን ለማረም የሚወጣውን ወጪና ጊዜ ይቆጥባል ነው የተባለው፡፡
ቴክኖሎጂው የተለያዩ ሲስተሞች የተጫኑበት ሲሆን ተማሪዎች ፈተናውን በሚወስዱበት ጊዜ የራሳቸው ታብሌት ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲስተም አለው ተብሏል።
ፈተናው የሚሰጥባቸው ታብሌቶችም በቅርቡ ለተማሪዎች እንደሚሰራጩ ተገልጿል።
ተማሪዎች ከቴክኖሎጂው ጋር እንዲተዋወቁ ከሶስት ሣምንት ያላነሰ ጊዜ የሚሰጣቸው ሲሆን ምንም ሳይጨናነቁ ለፈተና እንዲዘጋጁ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል - #MoE